የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤትክርስቲያን ሥረዓቶ ሰማያዊ ነው::"በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፥ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፥ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።"ራዕ11:19 እኛ ኦርቶዶክሳውያን አባቶቻችን የሰሩልን ሥረዓት ከሰማይ በማየት ነው በሰማይ መቅደስ አለ በምድርም እንዲሁ በሰማይ ታቦት አለ እንዲሁም በምድር .......ለዚህ ነው ሥረዓታችን ስማያዊ ነው ያልነው::ቅዱስ ነው የተለየ ለዓለም ነገር የማይውል ትልቅ ክብር አለው:: ከአሰራሩ ጀምሮ እስከ ሥም አሰያየሙ ምሥጢር አለው ትርጉም አለው::ይህን ላቆየልን ከምንም በላይ ለአምላክ ምስጋና ክብር ይግባው::በትውፊትም ላቀበሉን ጠንካራ አባቶቻችን ምስጋና ይሁንና እግዚአብሔርን የምናስብበት የክርስቶስን መከራ የምናስተውልበትን ሥርዓት ሰርተውልን አልፈዋል::ለዝህም ነው የቤትክርስቲያን ነዋየ ቅድሳት በቤተመቅደስ ብቻ የሚቀመጠው::
አንድ ታርክ ከመጽሃፍ ቅዱስ እናንሳ
"ንጉሡ ብልጣሶር ለሺህ መኳንንቶቹ ትልቅ ግብዣ አደረገ፥ በሺሁም ፊት የወይን ጠጅ ይጠጣ ነበር።ብልጣሶርም የወይን ጠጅ በቀመሰ ጊዜ ንጉሡና መኳንንቶቹ ሚስቶቹና ቁባቶቹ ይጠጡባቸው ዘንድ። አባቴ ናቡከደነፆር በኢየሩሳሌም ከነበረው መቅደስ ያመጣቸውን የወርቁንና የብሩን ዕቃዎች አምጡ ብሎ አዘዘ።የዚያን ጊዜም በኢየሩሳሌም ከነበረው ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የመጡትን የወርቁን ዕቃዎች አመጡ፤ ንጉሡና መኳንንቶቹም ሚስቶቹና ቁባቶቹም ጠጡባቸው።የወይን ጠጅም እየጠጡ ከወርቅና ከብር ከናስና ከብረት ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን አማልክት አመሰገኑ።በዚያም ሰዓት የሰው እጅ ጣቶች ወጥተው በንጉሡ ቤት በተለሰነው ግንብ ላይ በመቅረዙ አንጻር ጻፉ፤ ንጉሡም የሚጽፉትን ጣቶች አየ።የዚያን ጊዜም የንጉሡ ፊት ተለወጠበት፥ አሳቡም አስቸገረው፥ የወገቡም ጅማቶች ተፈቱ፥ ጕልበቶቹም ተብረከረኩ።ንጉሡም አስማተኞቹንና ከለዳውያኑን ቃላተኞቹንም ያገቡ ዘንድ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ንጉሡም የባቢሎንን ጠቢባን። ይህን ጽሕፈት ያነበበ ፍቺውንም ያሳየኝ ሐምራዊ ግምጃ ይለብሳል፥ የወርቅም ማርዳ በአንገቱ ዙርያ ይሆንለታል፥ በመንግሥትም ላይ ሦስተኛ ገዥ ይሆናል ብሎ ተናገረ።የዚያን ጊዜም የንጉሡ ጠቢባን ሁሉ ገቡ፤ ነገር ግን ጽሕፈቱን ያነብቡ፥ ፍቺውንም ለንጉሡያስታውቁ ዘንድ አልቻሉም።ንጉሡም ብልጣሶር እጅግ ደነገጠ፥ ፊቱም ተለወጠበት፥ መኳንንቶቹም ተደናገጡ።ንግሥቲቱም ስለ ንጉሡና ስለ መኳንንቱ ቃል ወደ ግብዣ ቤት ገባች፤ ንግሥቲቱም ተናገረች እንዲህም አለች። ንጉሥ ሆይ፥ ሺህ ዓመት ንገሥ፤ አሳብህ.........................
የዚያን ጊዜም ዳንኤል መለሰ በንጉሡም ፊት እንዲህ አለ። ስጦታህ ለአንተ ይሁን፥ በረከትህንም ለሌላ ስጥ፤ ነገር ግን ጽሕፈቱን ለንጉሡ አነብባለሁ ፍቺውንም አስታውቃለሁ።ንጉሥ ሆይ፥ ልዑል አምላክ ለአባትህ ለናቡከደነፆር መንግሥትንና ታላቅነትን ክብርንና ግርማን ሰጠው።ስለ ሰጠው ታላቅነት ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩም ቋንቋ የሚናገሩ ሁሉ በፊቱ ይንቀጠቀጡና ይፈሩ ነበር፤ የፈቀደውን ይገድል፥ የፈቀደውንም በሕይወት ያኖር ነበር፤ የፈቀደውንም ያነሣ፥ የፈቀደውንም ያዋርድ ነበር።ልቡ ግን በታበየ በኵራትም ያደርግ ዘንድ መንፈሱ በጠነከረ ጊዜ፥ ከመንግሥቱ ዙፋን ተዋረደ፥ ክብሩም ተለየው።ልዑል አምላክም በሰዎች መንግሥት ላይ እንዲሠለጥን፥ የሚወድደውንም እንዲሾምበት እስኪያውቅ ድረስ ከሰው ልጆች ተይለቶ ተሰደደ፥ ልቡም እንደ አውሬ ልብ ሆነ፥ መኖሪያውም ከምድረ በዳ አህዮች ጋር ነበረ፤ እንደ በሬ ሣር በላ፥ አካሉም በሰማይ ጠል ረሰረሰ።ብልጣሶር ሆይ፥ አንተ ልጁ ስትሆን ይህን ሁሉ እያወቅህ በሰማይ ጌታ ላይ ኰራህ እንጂ ልብህን አላዋረድህም።የመቅደሱንም ዕቃዎች በፊትህ አመጡ፥ አንተም መኳንንትህም ሚስቶችህም ቁባቶችህም የወይን ጠጅ ጠጣችሁባቸው፤ ከብርና ከወርቅም ከናስና ከብረትም ከእንጨትና ከድንጋይም የተሠሩትን የማያዩትንም የማይሰሙትንም የማያውቁትንም አማልክት አመሰገንህ፤ ትንፋሽህንና መንገድህን ሁሉ በእጁ የያዘውን አምላክ አላከበርኸውም።ስለዚህም እነዚህ የእጅ ጣቶች ከእርሱ ዘንድ ተልከዋል፤ ይህም ጽሕፈት ተጽፎአል።የተጻፈውም ጽሕፈት። ማኔ ቴቄል ፋሬስ ይላልየነገሩም ፍቺ ይህ ነው፤ ማኔ ማለት፥ እግዚአብሔር መንግሥትህን ቈጠረው ፈጸመውም ማለት ነው።ቴቄል ማለት፥ በሚዛን ተመዘንህ፥ ቀልለህም ተገኘህ ማለት ነው።ፋሬስ ማለት፥ መንግሥትህ ተከፈለ፥ ለሜዶንና ለፋርስ ሰዎችም ተሰጠ ማለት ነው።"ትንቢተ ዳንኤል 5:1-28
እንደተባለ በዛሬ ጊዜ የቤተመቅደሱን ንዋየ ቅድሳት ያለከልካይ ህገወጥ የሆኑ ሰዎች በየአዳራሹ በየሜዳው ይዘውት ይገኛል::ይህንን ደግሞ ማስቆም ያለብን እኛው ምዕመናን ብቻ ነን እኛ ማንንም አንጠብቅም ሥርዓታችን መፍረስ የለበትምና::ነዋየ ቅድሳት መጠብቅ በባለቤትነትም ማስከበር የኛ ፍንታ ነው::ሁላችንም እግዚአብሔርን ይዘን እማምላክን መከታ አድርገን በቅዱሳን ተደግፈን መስቀል ተመርኩዘን ወንጌልን ተጫምተን የሚያሸንፈን ማንም የለም::አትጠራጠሩ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና::ይህንንም ለማድረግ ምዕመናኑን ግንዛቤ ማስጨበጥ የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብና ምዕመናኑ መብቱን ራሱ ሌላ ሰው ወይም አካል ሳይጠብቅ እንዲያስከብር ማድረግ አለብን::ስለዚህም ይህንን ለምታገኙት ሰው አስተላልፉ በፌስቡክ ተወያዩ በብሎጎች ላይ ይውጡ::
እኛ እራሳችን ካልጠበቅነው ባለቤትነታችንን ካላስከበርነው ወደፊት ይህም መወሰዱ አይቀርም
"የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መብቶን እኛ ልጆቾ እናስከብር"
ነዋየ ቅዱሳቱ በረከሰ ቦታ እንዲወጡ አንፈቅድም
ይህንንም ለማድረግ ይረዳን ዘንድ ይህንን የፌስቡክ ግሩፕ ጆይን ያድርጉ ከርስዎ የሚጠበቅብዎትንም ያደርጉ
http://www.facebook.com/groups/280970945296065/members/#!/groups/280970945296065/28098263196156/?notif_t=group_activity
(የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤትክርስቲያን ነዋየ ቅድሳት እንጠብቅ በባለቤትነትም እናስከብር)
ለዚህም የጅማሬና የፍጻሜ ባለቤት የሆነው እግዚአብሄር ይርዳን የቅዱስ ያሬድ በረከቱ ና ጽናቱ አይለየን::
ቸር ይግጠመን
No comments:
Post a Comment