ESMEBEFKADU

Sunday, January 1, 2012

የሰው ማንነቱ አይደለም ውበቱ



የሰው ማንነቱ አይደለም ውበቱ 
ሐሰት ነው ውበቱ ደግሞም ደምግባቱ
ብቅል ሰቃይ ሎጋው ረጅም ቁመቱ 
ጠይም የቀይዳማ ደስ ደስ ያልው ፊቱ
ረጃጅም ጸጉር ፈርጣማ ደረቱ
ሰልከክ ያለ አፍንጫ ቁንጅና ውበቱ
ትላልቅ መኪና ቤት እና ንብረቱ
አይደለም ገንዘቡ ውበት ማንነቱ
አይደለም ውበቱ የሰው ማንነቱ
ሁሉም ነገር ረጋፊ የዓለም ነገር ከንቱ
ጠፊ ነው በሙሉ የሰው ልጅ ውበቱ
ሐይማኖት ምግባር ነው የሰው ልጅ ውበቱ
ማመን መታመን  ጠንካራ እምነቱ
ምግባር ጸባዩ ነው የሰው ልጅ ውበቱ
አዛኝ ለሰው ልጆች ገራገር ነው ልቡ
ውሸትና ሐሜት የሌለበት ተንኰል
ትሁት ሰውን ወዳጅ የማያውቅ በቀል
እሱ ነው የሰው ልጅ ማንነት ውበቱ
ገንዘብማ ከንቱ ውበት ደምግባቱ
ምግባር ሐይማኖት ነው የሰው ማንነቱ::




‎"ውበት ሐሰት ነው፥ ደም ግባትም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች::"ምሳ31:30
በዚህ ጥቅስ መሰረትነት የተገጠመ ግጥም::

2 comments:

  1. selam wendem alem yehenen getem lewuletegna gezie sanebewu des alegn bewunet betam wedejewalehu

    ReplyDelete