ቀኑ ዕለተ ሰንበት እሁድ መስከረም 21 , 2004 እጅግ የሚማርክ ቀን ነው:: ከተለያዩ ቦታዎች ተሰብስበው የጌታችን ግማደ መስቀልን ለማክበር እና ለመባረክ የመጡ ቁጥራቸው ብዙ እጅግ ብዙ ምዕመናን እንደ መላዕክት ነጭ በነጭ ለብሰው በየቦታው ጸሎታቸውን ያደርሳሉ::የቅዳሴው ጽሎት ካበቃ በኃላ ምዕመናኑ በያሉበት ቦታ ሁሉም እግዚአብሔርን በመዝሙር ያመስግናሉ ዝማሬ እጅግ ከልብ እና የማያቆርጥ ነው::ይህንን ከአመታት በኃላ በማየቴ እጅግ ተደሰቻለሁኝ::
መምህር ፍንታው በቃላቸው ታዓምረ ማርያምን ሲደግሙ
ታቦታቱ ከመንበሩ የሚንቀሳቀስበት በደረሰ ጊዜ ምእመናኑ በትውፊት በብሉይ ጊዜ አልያም በሃዲስ ኪዳን የዘንባባ ቅጠልን በሆሳዕና ጊዜ እንደ ተነጠፈ ስለተረዱት ና ስላወቁት እንዲሁም ያንን በተግባር በአገራችን በጥምቀት ጊዜ እንደለመዱት ምንጣፍ ማንጠፍ አልቻሉም::ከመካከላቸው አንድ እናት ለጌታዬ ምን የማይሆን የማይደረግ ነገር አለ ብለው ነጠላቸውን አውልቀው መሬት ላይ አንጠፉት ያ የተባረከ እና ታላቅ እምነት ያለው ህዝብ ነጠላውን በሙሉ አውልቆ ለታቦታቱ አነጠፈ የቃልኪዳኑም ታቦት ምዕመናኑን እየባረከ ወደ አውደ ምህረቱ ሄዱ::ታዲያ ይህ ታላቅ እምነት አይደል ..."እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ለሽማግሌዎች የተመሰከረላቸው በዚህ ነውና።ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን።አቤል ከቃየል ይልቅ የሚበልጥን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በእምነት አቀረበ፥ በዚህም፥ እግዚአብሔር ስለ ስጦታው ሲመሰክር፥ እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ ተመሰከረለት፤ ሞቶም ሳለ በመሥዋዕቱ እስከ አሁን ይናገራል።ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ፥ እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም። ሳይወሰድ እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተመስክሮለታልና፤ ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም"ዕብ11:1-6 እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ::
ታዲያ ይህንን ታላቅ እምነት ከፊታችን ባለው በጥምቀት ክብረ በዓል እንድሚደገም ጥርጥር የለኝም::

ምዕመናን ለታቦቱ ክብር የለበሱትን ነጠላ ሲያነጥፉ
ካህናቱ ወደ አውደ ምህረቱ ሲጎዙ
መልካም የጥምቀት በዓል
ቸር ይግጠመን
ቸር ይግጠመን
No comments:
Post a Comment