እያንገራገረ ህዝቡ እያባባ
አበው እያዘኑ ወጣት እያነባ
እየተቃወሙ እየጮሁ እነ አባ
ዜናው በዓለም ዓቀፍ እየተስተጋባ
ድንገት ሳይታሰብ ስኳር ገዳም ገባ
ከፍ ከፍ ብሎ ለዚያውም ዋልድባ
ሲጠፋ ሲሰወር ሲደበቅ ቆይቶ
በአቋሙ ጠንክሮ በአቋሙ ጸንቶ
አመክሮ ሳይዝ ድንገት ገዳም ገብቶ
ጣፋጭ የነበረው ሊመር ነው ከቶ
ለሱ የሚስማማ ስንት ቦታ ሞልቶ
ስኳር እሳት ሆኖ ከገበያ ጠፍቶ
ሊቀመጥ ነው አሉ መቃብር ቤት ገብቶ
ምን ይውጥሽ ይሆን ከእንግዲህ መርካቶ
አባቶች ምን አሉ በዋልድባ ያሉ
በአባቶች አጽም ላይ ሸንኮራን ሲተክሉ
ከተቀበረበት እየፈነቀሉ
በደም የበቀለ ሸንኮራ ሊበሉ
በውሳኔ ጸንቶ
ረ እግዚኦ በሉ!
ይሄስ ጥሩ አይደለም
ከአቅም በላይ ሆኖ ህዝቡ ቢበደለም
አባቶች ዝም በሉ ይረሱት ግድየለም
ዋልድባ በጾሙ ምነው ተፈተነ
በገዳሙ ልማድ ትንሽ ከታዘነ
ጽሎቱ እንደወጉ ከተከናወነ
ውሎ አድሮ ይሟሟል ስኳር ስለሆነ
ከአዜብ ሮባ
ምንጭ http://www.zehabesha.com/?p=5502
No comments:
Post a Comment