"እስመ በፈቃዱ ወበሥምረተ አቡሁ ወመንፈስ ቅዱስ መጽአ ወአድኅነነ"ውዳሴ ማርያም ዘሠሉስ
ESMEBEFKADU
Home
Monday, April 16, 2012
እኔስ በሃይማኖቴ እኔስ በእግዚአብሔር እመካለሁኝ ዓይኖቼ ማዳኑን አይተዋልና::
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰርዎ ለሰይጣን አግዓዝዎ ለአዳም
ሰላም እምይእዜሰ
ኮነ ፍስሐ ወሰላም
እንዼት ያስደስታል ይህንን በትንሣዔ ማየት ምንኛ ልብን ያስደስታል ከቅዱሳን መላዕክት ጋር ምስጋናን ማድረስ ...
ትንሣዔህን ለምናምን ለኛ ብርሃንን ላክልን ወደ እኛ
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት አትመረምር እጅግ ጥልቅ ናት::
Monday, April 9, 2012
ለከ ኃይል ክብር ወስብሓት ወዕዘዝ ለዓለመ ዓለም
"ለከ ኃይል ክብር ወስብሓት ወዕዘዝ ለዓለመ ዓለም።አማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሓት ወዕዘዝ ለዓለመ ዓለም።ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይል ክብር ወስብሓት ወዕዘዝ ለዓለመ ዓለም።ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብል በአኰቴት።"አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ..............."
ትርጉም፡-ኃይሌ መከታዬና ረዳቴ ለኾንከው ለአንተ ለአምላኬ ለአማኑኤል ለጌታዬ ለኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ክብርና ምስጋና ጽናትም ለዘላለም የአንተ ናቸው።እያልኩ"አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር ስምህም ይቀደስ............"
ይህን ሊንክ በመጫን ሙሉ ጸሎቱን ማዳመጥ የችላሉ
http://xa.yimg.com/kq/groups/12497888/1529139576/name/TheChantedPartofHolyWeekPrayers.mp3
ስብሓት ለእግዚአብሔር ኪያነ ዘፈጠረ ከመናምልኮ!
ስብሓት ለማርያም እመ አምላክ ንግሥትነ ወእምነ!
ስብሓት ለመስቀለ ክርስቶስ ዕፀ መድኃኒት፤ኃይልነ፤ወጸወንነ።
ትርጉም፡-
"እርሱን እናመልከው ዘንድ እኛን ለፈጠረ እግዚአብሔር ምስጋና ይጋባል።"
"አምላክን ለወለደች ለንግሥታችንና እናታችን ድንግል ማርያም ምስጋና ይጋባል"
"ኃይልና ጋሻ፤መድኃኒትም ለኾነን ለክርስቶስ በእንጨት ላይ ለመስቀሉ ምስጋና ይጋባል"
Wednesday, April 4, 2012
ኢየሱስ ክርስቶስ ካህኑ ለዓለም ንጉሠ ፅዮን ወንጉሰ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ
ኢየሱስ ክርስቶስ ካህኑ ለዓለም ንጉሠ ፅዮን ወንጉሰ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ
Jesus christ etrnal priest king of zion king of kings of Ethiopia
መድኃኒያለም ክርስቶስ በቀራኒዮ ስቁል
በለኒ መሃርኩከ በለኒ መሃርኩኪ
በእንተ ማርያም ድንግል እስመሔር አልቦ እንበሌከ ቃል
መድኃኒያለም የቸርነቱን ሥር ይስራልን::
ስኳር ገዳም ገባ
እያንገራገረ ህዝቡ እያባባ
አበው እያዘኑ ወጣት እያነባ
እየተቃወሙ እየጮሁ እነ አባ
ዜናው በዓለም ዓቀፍ እየተስተጋባ
ድንገት ሳይታሰብ ስኳር ገዳም ገባ
ከፍ ከፍ ብሎ ለዚያውም ዋልድባ
ሲጠፋ ሲሰወር ሲደበቅ ቆይቶ
በአቋሙ ጠንክሮ በአቋሙ ጸንቶ
አመክሮ ሳይዝ ድንገት ገዳም ገብቶ
ጣፋጭ የነበረው ሊመር ነው ከቶ
ለሱ የሚስማማ ስንት ቦታ ሞልቶ
ስኳር እሳት ሆኖ ከገበያ ጠፍቶ
ሊቀመጥ ነው አሉ መቃብር ቤት ገብቶ
ምን ይውጥሽ ይሆን ከእንግዲህ መርካቶ
አባቶች ምን አሉ በዋልድባ ያሉ
በአባቶች አጽም ላይ ሸንኮራን ሲተክሉ
ከተቀበረበት እየፈነቀሉ
በደም የበቀለ ሸንኮራ ሊበሉ
በውሳኔ ጸንቶ
ረ እግዚኦ በሉ!
ይሄስ ጥሩ አይደለም
ከአቅም በላይ ሆኖ ህዝቡ ቢበደለም
አባቶች ዝም በሉ ይረሱት ግድየለም
ዋልድባ በጾሙ ምነው ተፈተነ
በገዳሙ ልማድ ትንሽ ከታዘነ
ጽሎቱ እንደወጉ ከተከናወነ
ውሎ አድሮ ይሟሟል ስኳር ስለሆነ
ከአዜብ ሮባ
ምንጭ http://www.zehabesha.com/?p=5502
Monday, April 2, 2012
እስኪ ጎበዝ ቆም ብለን እናስብ ኢትዮጲያ ጣልያንን ያሸነፈችው ኃይለኛ ጣር ስላላት አይደለም ኃይለኛው አምላክ የሚማጽን ቅዱሳን ስላላት እንጂ
ኢትዮጲያዊ ሃብቱ ሳይሆን እምነቱ ና ባህሉ የአባቶቹ ጽሎት ነው እያኖረው ያለው::አመንም አላመንም የኛ በሰላም ውሎ ማደር ጤንነት ኑሮ በኛ ሃይል ብቻ የመጣ ሳይሆን እንደ እኛ አጥንትና ደም ሳይቆጥሩ ሌትከቀን በሚጸልዩት አባቶቻችን ጭምር የመጣ ነው::እስኪ ጎበዝ ቆም ብለን እናስብ ኢትዮጲያ ጣልያንን ያሸነፈችው ኃይለኛ ጣር ስላላት አይደለም ኃይለኛው አምላክ የሚማጽን ቅዱሳን ስላላት እንጂ:: ....
አበው እንዲህ ይላሉ ''መንግስት ሊወድቅ ሲያምረው ከታቦት ጋር ይጣላል''
...
"መብላት ቢያቅታት በተነችው"
...
ሳይቃጠል በቅጠል የዋልድባ ጉዳይ
Newer Posts
Older Posts
Home
Subscribe to:
Posts (Atom)