ESMEBEFKADU

Monday, September 24, 2012

ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።ገላ6፤14

"ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።"ገላ6፤14

መስቀል መመኪያችን ነው።
የቤተክርስቲያን ልጆች መስቀልን የምንሳለመው፤የምናከብረው፤የምንሳለመው፤የምንሰግደው፤መመኪያችን ስለሆነ ነው።መስቀልን በአንገታችን ላይ የምናጠለጥለው በልብሳችን ላይ እንደ ጌጥ የምናደረገው መስቀል መመኪያችን ስለሆነ ነው።በመስቀል መመካት የተማርነው ከቅዱሳን ነው።"ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።"ገላ6፤14 በማለት ቅ/ጳውሎስ ተናግሮል።ከዚህ የተነሳ ነው እኛ ኢትዮጲያን በየትኛውም ዓለም ብንኖር መስቀልን መመኪያ አድርገን የምንጕዘው።
በመስቀል መመካት፤መባረክ፤መስገድ፤ለአለሙ ሞኝነት ይመስለዋል።1ኛቆሮ1፤18"የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።"ነገረ መስቀሉ የ እግዚአብሔር ሀይል የሚገለጥበት መሆኑን ቅዱስ ጳውሎስ ነግሮናል።ለቅዱስ መስቀሉም መስገድ እንደሚገባን ይነግረናል።መዝ13፡7"እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን።"ጌታችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእለተአርብ በመስቀል ላይ ተሰቅሎልና።
ጠላታችንንም ድል የምናደርግበት በመስቀል ነው።"ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ፥ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው። "መዝ59፤4 ምልክት የተባለው የመስቀል ምልክት ነው።በመስቀል ከሰይጣን እንደምንድን ሲነግረን ነው።
እርግማችን ተወግዶ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ ይሰጠን ዘንድ በመስቀል ተሰቀለ ።ስለዚህ መስቀል እርግማናችንን አጥፍቶ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ ይስጠናል።
መስቀል ዲያቢሎስ የተሸነፈበት የተዋረደበት ነው።"ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው። "ኤፌ2፤16 ጥልን ወይም ጸብን በመስቀሉ ገደለ ሲል፡- ጥልን ወይም ጸብን የሚዘራና የሚያመጣ ዲያቢሎስን ገደለ ሲል ነው።ዲያቢሎስ ሰውን ከ እግዚአብሔር ሁል ጊዜ ያጣላል ስለዚህ ነው ጥልን በመስቀሉ ገደለ ያለው።

መስቀሉን ስናይ እ ገዚአሔር ምን ያህል እንደወደደን እናውቃለን እስከ መስቀል ሞት ድረስ ወዶናልና።

ሰውና መላእክት የታረቁት በመስቀል ላይ በተፈጸመ ቤዛነት ነው።


የመስቀሉ ረድኤት በረከት በእኛ ላይ ይደር።


ደመራ በ5 ክርስቲያኖች ሲደመር


መስከረም 16 ቀን 2004 ዓም ነው በሰሜን የኢትዮጲያ ክፍል በሰሜን ውሎ ውልድያ ከተማ::ከጧቱ 11ስዓት ነው  የወፎቹ ዜማ ከጧቱ ብርድ ጋር ተቀላቅሎ ውስጣችን ዘልቆ ይሰማናል::እንደሌሎቹ ተጓዦች እኔ ና 3 ጓደኞቼ በረንዳ ላይ ምንጣፍ ተነጥፎልን ነበር ያደርነው ምክነያቱም የወ/ሮ በላይነሽ ቤት 60 ሰው የመያዝ አቅም ስሌላት በረንዳው ግን ለጥ ያለነው::መንፈሳዊ ጉዞ ታላቅ ፍቅርን ያስተምራል መተጋገዝን መረዳዳትን ያሰተምራል በጧት ተቀሳቅሰን ወደ ባሳችን አያመራን ነው::በባስ ውስጥ ያለነው 62 መንፈሳዊ ተጓዦች ነን ከአርባምንጭ ከተማ ተነስተን በደ/ሊባኖስ,ጣና ገዳማት ጎንደር , አክሱም , ደ/ዳሞ ,ቅ/ላሊበላ,ቅድስአርሴማ,... አገባደን ይህው ዛሬ እዚህ የደረስነው:: ሁሉም ከእንቅልፍ ተቀሳቅሶ ለጉዞ ተዘጋጀ ::እንደተለመደው በባሱ ውስጥ ጸሎት ለማድረግ ቦታ ቦታችንን ይዘናል::የጉዛችን አስተባባሪ ዓለሙ እይደጋገመ የቀሩ እናቶችን በመደገፈ ወደ መኪናው ያስገባል::ጉዛችን በጽሎት እንደተለመደው ተከፈተ በአባ ቦረዳ (ቆሞስ አባ ገ/ማርያም) ከዝያም በመቀጠል ተዓምረ ማርያም ተነበበ::የ አባ ቦረዳ የተዓምር አነባበብ ቅላጼው ለየት ያለና የሚማርክ ነው በ እውነት ውስጤን ይነካኛል ለዚህም ነው ሁልጊዜ ተዓምር ሲነበብ መጽሃፉን ለአባ ለመያዝ የሚቀድመኝ የለም::አባን በማየት ብቻ በጣም ብዙ ትምህርት ማግኘት ይቻላል እኔ ነኝ በዚህ ጉዞ አባ ምን ያህል እንዳስተማሩኝ የማውቀው::ስለ አባ ለማወቅ ቀርቦ ያያቸው ሰው ያውቀዋል ምስክሩም እሱ ነው::አባን እግዚአብሔር ይጠብቅልን::ቀጥታ ጸሎቱ እንዳበቃ ወደ ማመጫ ተክለሐይማኖት ጉዞ አደረግን::ስለ ማመጫ ተክለሐይማኖት በሌላ ጊዜ በሰፊው ብተርከው ሳይሻል አይቀርም::ወደዛሬ ጉዳዬ ስመጣ የማመጫ ጉዞ ቀትር ላይ ከተጠናቀቀ በኃላ ነው ሁለተኛ የ ደመራ ፕሮግራም ወደ ሐራ ማርያም ያደረግነው::ሐራ ትንሽ ከተማ ስትሆን የከተማዋ ነዋሪዎች በሙሉ ከ 5 ክርስቲያን በስተቀር ሙስሊም ናቸው::ሐራ ማርያም ከተማው መሐል ጉብ ብላ በአህዛብ መካከል ነግሳለች ይህንን በማሰብ ነበር የጉዛችን አስተባባሪ ደመራን ከእነሱ ጋር እንድናከብር ያመቻቹልን ጉዞ ወደ ሐራ ማርያም::መኪናችን ከተማው ሲገባ በዝማሬ ነበር ሁሉም ምዕመን ነጭ በነጭ ልብሰናል ዝማሬው አላቋረጠም::የከተማው ነዋሪዎች ገርሟቸው በግርምት ይመለከቱናል::በከተማው መኃል በዝማሬ ታጅብን ወደ ቤተክርስቲያኑ አመራን አዲሱ ቤተክርስቲያን ለመስራት ከተጀመረ ዘመን የለውም በተለያየ ምክነያት ሳይፈጽም ቀርቶ አሁነም እያየነው ነው:: እነዚያ በሰቆቃ የነብሩ በብቸኝነት የነበሩ ምዕመናን ከደስታቸው ብዛት በዕንባ ተቀበሉን የሚያደርጉልን ጠፋ::1 ዲያቆን እና 1ካህን ነው ያሉት ከቤተመቅደስ ነዋየቅዱሳቱን ይዘው ወጡ ቃጭል ተመታ መስቀልም ተያዘ ጉዞ ወደ መስቀል አደባባይ(አንድ የክርስቲያን ግቢ ውስጥ) ደመራ ተደመረ ምስባኩም ተሰበከ በአባ ቦረዳ ጣዕምያለው አጥንትን የሚያለመልም ትምህርትን ተማርን ደመራው ተለኮሰ ዛሬ 67 ሆነን ደምራውን አክበርን::እንዴት ደስ ይልነበር በጣም እንጂ ደምራን ከ ነዚያ ምዕመን ጋር ማሳለፍእጅግ ደስ ያሰኛል ወገን አጥተው በብቸኘነት ካሉ እንድዚህ አየንት ችግር ያለባቸው ደምራን ጥምቀትን የማያክብሩ ስንት ደብሮች ስንት ገዳማት በችግር ምክነያት እንደታጓሉ... ቤት ይቁጠረው እንዲህ አይነት ችግር ያሉበት ቦታዎች ::በዚህን ጊዜ ነበር የ አዲስ አበባው መስቀል አደባባይ አልያም ጊሸን ደ/ከርቤ የሚከበረው ትዝ ያለኝ::በብዙ ምዕመን መሃል ሆኖ ማክበር ደስ ቢልም በትንሽ ሰዎችህ መሃል በ እንባ በተቀላቀለበት ስሜት ማክበር ደግሞ ስሜትን ያስደስታል እጅግም ደስ ይላል እነሱ በደስታቸው ሲለቅሱ ማየት እኛ ከእነሱ ጋር እግዚአብሔርን ስናመሰግን ስላዩ ብቻ ሲደስቱ ማየት እንዴት የሚገርም ክርስትና ነው::
ድሮ ደመራ በ 5ክርስቲያንች ሲደመር ነበር ባልፈው ዓመት በ 67 ሰው  ተከበሮል ዝንድሮስ እንዴት ያከብሩ ይሆን ???
እስቲ የዛሬ ዓመቱን ፊልምና ፎቶው ልጋብዛችሁና ልሰናበት በጽሎታችሁ አስቧቸው::










to watch the vidio on facebok use this link ይህንን ይጫኑ



Tuesday, September 11, 2012

እመቅደመ ዘመናት ዘመናዊ ደኅረ ዘመን ሀዲስ ኢየሱስ ናዝራዊ::"


የ እግዚአብሔር ሥራው እንዴት ድንቅ ነው?ዘመናት የሌለው ከዘመናት በፊት የነበረ ያለ እና ወደ ፊትም የሚኖር ፈጣሪያችን ዘመናትን አቀናጀን የ እግዚአብሔር ሥራው እንዼት ድንቅ ነው::እሰከዚህ ሰዓት አድርሶናልና ምስጋና ይገባዋል::
"
ከዘመናት በፊት አንተ ነበርክ ሁሉን አሳልፈህ ትኖራለህ::
እመቅደመ ዘመናት ዘመናዊ ደኅረ ዘመን ሀዲስ ኢየሱስ ናዝራዊ::"
እመቅደመ ዘመናት ዘመናዊ ደኅረ ዘመን ሀዲስ ኢየሱስ ናዝራዊ::"

አወዳ ዓመን በባዕድ አገር ማሳለፍ እንደምን ልብን ይነካል በተለይ አገር ቤትን ባሰብኩኝ ቁጥር በአዕምሮዬ ብዙ ነገር ይመጣል የአውዳመት ሽታውም ይሸታል::በባዕድ አገር ወዼት አለ የ አወዳመት ሽታው? ወዴት አለ እንጀራ እና ወጡ ወዴት አለ ጣላ እና ጠጁ ወዴት አለ ዘመድ ጥየቃው ወዴት አለ የቤተሰብ ስብስቡ ወዴት አለ የቤተሰብ ስብስቡ ይህንን ባሰብኩኝ ቁጥር ወደ አገሬ በርሬ በሃሳብ ሄድኩኝ ከእናት አባቴ ጋር በላሁኝ ጠጣሁኝ ከጎደኞቼ ጋር ተጫወትኩ ደስም ተሰኘሁኝ::ከሃሳቤ ስነቃ እንባን በአይኔ አገኜሁኝ::


መልካም አወዳመት

Monday, June 18, 2012

እንኳን ለታላቁ መላክ ለቅዱስ ሚካኤል ንግስ አደረሳችሁ::
አማልደን ኃያሉ መላክ!!!
ባህራንኒ

Tuesday, May 1, 2012

አዲስ ሐዋርያ ብርሃን ዘኢትዮጲያ አባታችን ተክለሐይማኖት


ብዙ ፃድቃን ብታይም በዘመኖ ኢትዮጽያ 
እንዳንተ አላየችም ሐዲስ ሐዋርያ
የብዙወች አባት መምህር መጠጊያ
ፃድቁ ተወልደ ከፀጋ ዘአብ ከእግዚሐርያ።
ቅዱስ ሚዳኤል ሊቀ መላእክት 
ይመራውም ነበር ከኃላ ከፊት።
ምድራዊ መላእክ የመረጡት ስላሴ
የዓለም ቡራኬ ዳግማዊ ሙሴ
አለምን የናቀ ፅኑ መነኩሴ።
ፀጋ የተሰጠው የድህነት የፈውስ
ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ።
የዓለም ፀሀይ የገዳም መብራት 
የእቲስ አንበሳ ተክለሃይማኖት።
ገድልህ ሲነበብ ታምርህ ሲነገር
እፁብ ድንቅ ያሰኛል የተሰጠህ ክብር።
ጠንቆይ አጋንቱን በእምነት ደመሰሰ
ወንጌልን አስተምሮ ፍቅር አነገሰ።
ብርሃን ፈንጣቂው የጨለማ ጠላት
የድህ ድል ምድራዊ ሀብት።
የፀሎቱ ሀይል ጥልቅ ነው ሚስጥሩ
ስድስት ክንፍ አወጣ ቢቆረጥ አንድ እግሩ።
ተነጥቆ ወደ ሰማይ በአምላክ ተባርኳል
በሱራፌል ተርታ ቅዱስ ቅዱስ ይላል።
ገዳምህ ተባርኳል በእየሱስ ክርስቶስ
ምህረት ይታፈሳል በደብረ ሊባኖስ።
ስለ ሀይማኖቱ ከወርቅ የነጠረ
በሰማይ በምድር ተክሌ ከበረ።
ቃልኪዳንህን እኛም እናምናለን
አማልደን አደራ ከቸር አምላካችን 
ዋስ ጠበቃ ሁነን ተክልዬ አባታችን።




ምንጭ :http://www.youtube.com/watch?v=mgqZENrY7oY

Monday, April 16, 2012

እኔስ በሃይማኖቴ እኔስ በእግዚአብሔር እመካለሁኝ ዓይኖቼ ማዳኑን አይተዋልና::


ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን     በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰርዎ ለሰይጣን                  አግዓዝዎ ለአዳም
ሰላም                                እምይእዜሰ
ኮነ                                   ፍስሐ ወሰላም


እንዼት ያስደስታል ይህንን በትንሣዔ ማየት ምንኛ ልብን ያስደስታል ከቅዱሳን መላዕክት ጋር ምስጋናን ማድረስ ...

ትንሣዔህን ለምናምን ለኛ ብርሃንን ላክልን ወደ እኛ


ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት አትመረምር እጅግ ጥልቅ ናት::

Monday, April 9, 2012

ለከ ኃይል ክብር ወስብሓት ወዕዘዝ ለዓለመ ዓለም

"ለከ ኃይል ክብር ወስብሓት ወዕዘዝ ለዓለመ ዓለም።አማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሓት ወዕዘዝ ለዓለመ ዓለም።ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይል ክብር ወስብሓት ወዕዘዝ ለዓለመ ዓለም።ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብል በአኰቴት።"አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ..............."
ትርጉም፡-ኃይሌ መከታዬና ረዳቴ ለኾንከው ለአንተ ለአምላኬ ለአማኑኤል ለጌታዬ ለኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ክብርና ምስጋና ጽናትም ለዘላለም የአንተ ናቸው።እያልኩ"አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር ስምህም ይቀደስ............"
ይህን ሊንክ በመጫን ሙሉ ጸሎቱን ማዳመጥ የችላሉ
http://xa.yimg.com/kq/groups/12497888/1529139576/name/TheChantedPartofHolyWeekPrayers.mp3
ስብሓት ለእግዚአብሔር ኪያነ ዘፈጠረ ከመናምልኮ!
ስብሓት ለማርያም እመ አምላክ ንግሥትነ ወእምነ!
ስብሓት ለመስቀለ ክርስቶስ ዕፀ መድኃኒት፤ኃይልነ፤ወጸወንነ።
ትርጉም፡-
"እርሱን እናመልከው ዘንድ እኛን ለፈጠረ እግዚአብሔር ምስጋና ይጋባል።"
"አምላክን ለወለደች ለንግሥታችንና እናታችን ድንግል ማርያም ምስጋና ይጋባል"
"ኃይልና ጋሻ፤መድኃኒትም ለኾነን ለክርስቶስ በእንጨት ላይ ለመስቀሉ ምስጋና ይጋባል"


Wednesday, April 4, 2012

ኢየሱስ ክርስቶስ ካህኑ ለዓለም ንጉሠ ፅዮን ወንጉሰ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ


ኢየሱስ ክርስቶስ ካህኑ ለዓለም ንጉሠ ፅዮን ወንጉሰ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ
Jesus christ etrnal priest king of zion king of kings of Ethiopia

መድኃኒያለም ክርስቶስ በቀራኒዮ ስቁል
በለኒ መሃርኩከ በለኒ መሃርኩኪ
በእንተ ማርያም ድንግል እስመሔር አልቦ እንበሌከ ቃል


መድኃኒያለም የቸርነቱን ሥር ይስራልን::

ስኳር ገዳም ገባ

እያንገራገረ ህዝቡ እያባባ 
አበው እያዘኑ ወጣት እያነባ
 እየተቃወሙ እየጮሁ እነ አባ 
ዜናው በዓለም ዓቀፍ እየተስተጋባ 
ድንገት ሳይታሰብ ስኳር ገዳም ገባ
ከፍ ከፍ ብሎ ለዚያውም ዋልድባ 
ሲጠፋ ሲሰወር ሲደበቅ ቆይቶ 
በአቋሙ ጠንክሮ በአቋሙ ጸንቶ
አመክሮ ሳይዝ ድንገት ገዳም ገብቶ 
ጣፋጭ የነበረው ሊመር ነው ከቶ 
ለሱ የሚስማማ ስንት ቦታ ሞልቶ 
ስኳር እሳት ሆኖ ከገበያ ጠፍቶ 
ሊቀመጥ ነው አሉ መቃብር ቤት ገብቶ 
ምን ይውጥሽ ይሆን ከእንግዲህ መርካቶ 
አባቶች ምን አሉ በዋልድባ ያሉ
በአባቶች አጽም ላይ ሸንኮራን ሲተክሉ
ከተቀበረበት እየፈነቀሉ
በደም የበቀለ ሸንኮራ ሊበሉ
በውሳኔ ጸንቶ 
ረ እግዚኦ በሉ!
ይሄስ ጥሩ አይደለም
ከአቅም በላይ ሆኖ ህዝቡ ቢበደለም
አባቶች ዝም በሉ ይረሱት ግድየለም
ዋልድባ በጾሙ ምነው ተፈተነ
በገዳሙ ልማድ ትንሽ ከታዘነ
ጽሎቱ እንደወጉ ከተከናወነ
ውሎ አድሮ ይሟሟል ስኳር ስለሆነ


ከአዜብ ሮባ 



ምንጭ http://www.zehabesha.com/?p=5502

Monday, April 2, 2012

እስኪ ጎበዝ ቆም ብለን እናስብ ኢትዮጲያ ጣልያንን ያሸነፈችው ኃይለኛ ጣር ስላላት አይደለም ኃይለኛው አምላክ የሚማጽን ቅዱሳን ስላላት እንጂ


ኢትዮጲያዊ ሃብቱ ሳይሆን እምነቱ ና ባህሉ  የአባቶቹ ጽሎት ነው እያኖረው ያለው::አመንም አላመንም የኛ በሰላም ውሎ ማደር ጤንነት ኑሮ በኛ ሃይል ብቻ የመጣ ሳይሆን እንደ እኛ አጥንትና ደም ሳይቆጥሩ ሌትከቀን በሚጸልዩት አባቶቻችን ጭምር የመጣ ነው::እስኪ ጎበዝ ቆም ብለን እናስብ ኢትዮጲያ ጣልያንን ያሸነፈችው ኃይለኛ ጣር ስላላት አይደለም ኃይለኛው አምላክ የሚማጽን ቅዱሳን ስላላት እንጂ::     ....

አበው እንዲህ ይላሉ ''መንግስት ሊወድቅ ሲያምረው ከታቦት ጋር ይጣላል''
...
"መብላት ቢያቅታት በተነችው"
...
ሳይቃጠል በቅጠል የዋልድባ ጉዳይ



Tuesday, March 13, 2012

አንተ ባለህበት


ምንም በደል  ቢኖር
         
ኃጢአትም ቢበዛ
የመታዘዝ ፍሬ
        
ከሰዎች ቢታጣ
የፅድቅ ሥራ  ጠፍቶ
         
አመፅ ቢበረታ
አንተ ባለህበት ---
          
በዚያ ምህረት አለ
          
ኩነኔም  የለበት
የሚያስደንቅ ማዳን
          
ፍቅር የሞላበት
የይቅርታ ጉዞ
           
ፅድቅ የሰፈነበት
---
ምን ጠላት ቢበዛ
           
ኃይሉም ቢበረታ
ቀንበሩም  ቢፀና
              
ቢበዛም ሁካታ
አስፈሪ ነበልባል
              
እጅግ ቢንበለበል
ውኃውም ቢፈላ
             
ቢፍለቀለቅ በኃይል
የኤርትራ ባህር
              
በሰፊው ቢንጣለል
ወደ አንበሶች ጉድጉዋድ
               
ቢኖር እንኳን መጣል
አንተ ባለህበት ---
             
ጠላት ይሸነፋል
የእብሪቱ  ድልድይ
              
በቃልህ ይናዳል
ነፃነት ታውጆ
             
ቀንበሩም ይነሳል
ፍል ውሃው ቀዝቅዞ
              
እሳቱም ይጠፋል
ባህሩ እንደተራራ
             
ቀጥ ብሎ ይቆማል
ጠላት ከነጀሌው 
              
በውሃ ይበላል
              
ውሃ ውስጥ ይሰጥማል
የአናብስቱም አፍ
               
በኃይልህ ይዘጋል
--- 
ነውጡ እጅግ ቢያይል
               
ማእበል ቢነሳ 
ተስፋ መቁረጥ ነግሶ
                
ቢበዛም አበሳ
አንተ ባለህበት ---
                
ይታዘዛል ባህሩ
ነውጡም ያጣል ኃይሉን
               
ጸጥ ይላል ማእበሉ
---
አሳዎች በባህር
               
አንዳችም ባይኖሩ
መረቡም ባይሞላ
               
ድካም ቢሆን ትርፉ
አንተ ባለህበት
               
ማጣት የለም ከቶ
ረሃብ ይወገዳል
                
አሳው ተትረፍርፎ
                
መረቡም ሞልቶ
---
ህመም ደዌ ጸንቶ
                 
ሕይወት ብትደበዝዝ
አስታማሚ ጠፍቶ
                  
ባይኖርም የሚያግዝ
አንተ ባለህበት ---
                
መድሃኒት መች ጠፍቶ
የማያየው ሁሉ
                  
ይመለሳል አይቶ
በደስታ ይቦርቃል
                  
ለምፃሙ ሰው ነፅቶ 
ዲዳው ይናገራል
                 
ይጮሃል አብዝቶ
---
ምን ሞት ቢበረታ
                  
ቢያይል ፍርሃቱ
ብቸኝነት ነግሶ
                  
ቢበዛ ጭንቀቱ
አንተ ባለህበት ---
            
ሞት ስልጣኑን ያጣል
ማንቀላፋት የለም
             
የሞተም ይነሳል
ሀዘኑ በደስታ
              
ሞትም በትንሣኤ
              
በአንተ ይለወጣል
ስለዚህ ጌታ ሆይ
             
በአንተ ሁሉ ካለ
የአንተ ልሁንና
             
ሁሉን ላግኝ  ከአንተ

መቅደስ አያሌው  (ከደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን)

Wednesday, February 29, 2012

ስለ ጥንታዊው የሃይማኖት ዩኒቨርስቲ ሐይቅ እስጢፋኖስ አባ እየሱስ ሞዐ ገዳም በብጽኡ አብነ አትናቲዎስ


ስለ ጥንታዊው የሃይማኖት ዩኒቨርስቲ ሐይቅ እስጢፋኖስ አባ እየሱስ ሞዐ ገዳም በብጽኡ አብነ አትናቲዎስ አንደበት እነሆ (ይህንን ሊንክ ይጫኑት ለማየት http://www.ustream.tv/recorded/20717258)

ይህ ታላቅ ገዳም በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ በ862 ዓ.ም የተመሰረተ ነው::  አባታችን አብነ ተክለሐይማኖት ያገለገሉበት ቦታ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተማሩበት ያገለገሉበት ታላቅ ገዳም ነው::

"የሰው ልጅ ሃገሩ ሃይማኖቱ ነው ሃብቱ ንብረቱም ልጅነቱ ነው:: የሰው ልጅ ከሃይማኖቱ እስካልወጣ ድርስ ስደተኛ አይደለም::"ብጽኡ አብነ አትናቲዎስ የደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ


ከቦታው ረደኤት በረከት ይድረሰን የአባቶቻችን ጸሎት ሁልጊዜ ይርዳን አሜን::

Friday, February 24, 2012

ድንግል ማርያም እሙ ወእምነ ንግሥተ ፅዮን ወንግሥተ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ

ድንግል ማርያም እሙ ወእምነ ንግሥተ ፅዮን ወንግሥተ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ

The Virigin Mary Mother of GOD and our holy Mother Queen of Zion and Ethiopia 
ከእመቤታችን ከቅድስት ኪዳነምህረት ረድኤት በረከት ያሳትፈን::

"ያለ በጎ ሥራ የምጽድቅ መንግስተ ሰማያትንም የማልወርስ ከሆነ እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ቃልኪዳንሽ ለከንቱ ነበርን"
እግዚአብሔር አምላካችን የምህረት ቃልኪዳኑን አስቦ ይማረን:: 



Saturday, January 28, 2012

ትንኝን ማጥራት ግመልን መዋጥ


                       ትንኝን ማጥራት ግመልን  መዋጥ   ማቴ 23
  • ሁሌ እኔ ቤተክርስቲያን ሳለስቀድስ ስቀር ተቸግሬ ነው::ሌላው ሠው ሲቀር ግን ደካማ ለቤተክርስቲያን ቀናኢ አስተሳሰብ የሌለው ሆኖ ነው::
  • ሠውን ሳማና ስተች ከእውነት ከልብ ከመነጨ ቅን አስተሳሰብ ነው::ሌሎች ሲሆኑ ግን ሐሜቶኞች ወሬኛ ሠው አናጋሪ ነገር ለቃሚዎች ናቸው::
  • እኔ ቤተክርስቲያን ውስጥ ስስቅ ስቀልድና ስዘልፍ ከጓደኛዬ ጋር እየተጫወትኩኝ ነው::ሌሎች ሲሆኑ ግን የቤተክርስቲያን ህግ እና ሥርዓት እየጣሱ ነው::
  • እኔ ሳልጻም ሳልጸልይ ቤተ እግዚአብሔር ሳልሄድ ሳልሰግድ ስቀር ሕመሜን የልቤን ችግር እግዚአብሔር ተረድቶት ነው::ሌሎች ሲሆኑ ግን ሰነፎች አስመሳይ ክርስቲያኖች ሆነው ነው::
  • እኔ ጠጥቼ ስሰክር ስዳንስ ስጨፍር ሳጨስ ትንሽ የሥጋ ድካም ተሰምቶኝ ነው::ሌሎቹ ሲሆኑ ግን የቤተክርስቲያን ማንነት አሰዳቢ ናቸው::
  • እኔ ጠንቆይ ቤት ስሄድና ሳስጠነቁል ጨሌ አቴቴ ሳደርግ ፅንስ ሳስወርድ ጨንቆኝ የማደርገው ጠፍቶኝ ነው::ለሎች ሲሆኑ ግን ጣኦት አምላኪዎች ነፍሰ ገዳዬች ናቸው::
  • እኔ ሳመነዝር የትዳር ጓደኛ ለመምረጥ ጥረት እያደረኩ ነው::ደግሞም እኮ እግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙላአት የሚለውን ቃል እየፈጸምኩኝ ነው:: ሌሎች ሲሆኑ ግን ሴሰ ሆነው ነው::
  • እኔ ለድሃ ምፅዋት ስሰጥ ራርቼ አዝኜ ችግራቸው እኔ ችግር ሆኖ ነው::ሌሎች ሲሆኑ ግን ሀብታቸውን ንብረታቸውን ለሰው ሊያሳዩ ለታይታ ነው::
  • እኔ ጉቦ ስበላና ስሰርቅ ቸግሮኝ ኑሮዬን ለማሸነፍ ጥረት እያደረኩ መሆኑን እግዚአብሔር የልቤን ችግር ስለሚያውቅ ነው:: ሌላው ግን ጉቦኛ ሌባ ሆኖ ነው::
  • እኔ ስጾም ስጸልይ ጻድቅ ትሑት ሆኜ   የእግዚአብሔር ፍቅር አሸንፎኝ ነው::ሌላው ሠው ሲሆን ግን የሚሠራውን ሲያጣ የረሃብ አድማ በራሱ ላይ እያደረገ ነው::
  • እኔ ጠዋት እንቅልፍ ይዞኝ ሥርዓተ-ቅዳሴ  እንደተጀመረ ቤተክርስቲያን ስገባ ምንም አይደለም እግዚአብሔር እንደ ደከመኝ ያውቃል::ሌላው ሲሆን ግን የእግዚአብሔርን መላእክት እየረገጠ መግባቱና ሥርዓት ማፍረሱ ነው::
  • እኔ ቤተእግዚአብሔር ጉባዔ ስቀር በጣም ሥራ በዝቶብኝ ጊዜ አጥቼ ነው::ሌሎች ሲሆኑ ግን እግዚአብሔር እየራቁና አየሰነፉ መምጣታቸው ነው::
  • እኔ ቤተክርስቲያን ቀር ሠርግ ድግስ ዘመድ ጥየቃ ስሄድ ሠው ብቻውን ያለሠው መኖር እንደማይቻል ራሱ እግዚአብሔር ጠንቅቆ ስለሚያውቀው ነው::ሌሎች ሲሆኑ ለቤተክርስቲያን ቅናት ተቋርቋሪነት ፈፅሞ የሌላቸው ከንቱዎች ሆነው ነው::

ታዲያ የራስን ኃጢያት በመልካም ሥም ከማሞካሸት ተመልሼ የሌላውን ኃጢያት በባትሪ ፈልጌ ከመንቀስ ተቆጥቤ ግመልን ውጬ ትንኝን አጥርቼ ትንሿን የአፈር ክምር ተራራ ማሣከል ትቼ ራሴን ማስተካከል እንድጀምር እግዚአብሔር ይርዳኝ::


የማቴዎስ ወንጌል 23
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለሕዝቡና ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብሎ ነገራቸው። ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል።ስለዚህ ያዘዙአችሁን ሁሉ አድርጉ ጠብቁትም፥ ነገር ግን እየተናገሩ አያደርጉትምና እንደ ሥራቸው አታድርጉ። ከባድና አስቸጋሪ ሸክም ተብትበው በሰው ትከሻ ይጭናሉ፥ እነርሱ ግን በጣታቸው ስንኳ ሊነኩት አይወዱም።ለሰውም እንዲታዩ ሥራቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ስለዚህ አሽንክታባቸውን ያሰፋሉ ዘርፉንም ያስረዝማሉ፥ በምሳም የከበሬታ ስፍራ፥ በምኵራብም የከበሬታ ወንበር፥በገበያም ሰላምታና። መምህር ሆይ መምህር ሆይ ተብለው እንዲጠሩ ይወዳሉ።እናንተ ግን። መምህር ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ። አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም። አባት ብላችሁ አትጥሩ። ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና። ሊቃውንት ተብላችሁ አትጠሩ። ከእናንተም የሚበልጠው አገልጋያችሁ ይሆናል።ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል።እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ፥ ወዮላችሁ እናንተ አትገቡም የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በጸሎት ርዝመት እያመካኛችሁ የመበለቶችን ቤት ስለምትበሉ፥ ወዮላችሁ፤ ስለዚህ የባሰ ፍርድ ትቀበላላችሁ።እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ አንድ ሰው ልታሳምኑ በባሕርና በደረቅ ስለምትዞሩ፥ በሆነም ጊዜ ከእናንተ ይልቅ ሁለት እጥፍ የባሰ የገሃነም ልጅ ስለምታደርጉት፥ ወዮላችሁ።እናንተ። ማንም በቤተ መቅደስ የሚምል ምንም የለበትም፤ ማንም በቤተ መቅደስ ወርቅ የሚምል ግን በመሐላው ይያዛል የምትሉ፥ ዕውሮች መሪዎች፥ ወዮላችሁ።እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች፥ ማናቸው ይበልጣል? ወርቁ ነውን? ወይስ ወርቁን የቀደሰው ቤተ መቅደስ? ደግማችሁም። ማንም በመሠዊያው የሚምል ምንም የለበትም፤ ማንም በላዩ ባለው መባ የሚምል ግን በመሐላው ይያዛል ትላላችሁ። እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች፥ ማናቸው ይበልጣል? መባው ነውን? ወይስ መባውን የሚቀድሰው መሠዊያው? እንግዲህ በመሠዊያው የሚምለው በእርሱና በእርሱ ላይ ባለው ሁሉ ይምላል፤ በቤተ መቅደስም የሚምለው በእርሱና በእርሱ በሚኖረው ይምላል፤በሰማይም የሚምለው በእግዚአብሔር ዙፋንና በእርሱ ላይ በተቀመጠው ይምላል።እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥ ወዮላችሁ፤ ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር።
እናንተ ዕውሮች መሪዎች፥ ትንኝን የምታጠሩ ግመልንም የምትውጡ።እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውስጡ ቅሚያና ስስት ሞልቶ ሳለ የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ስለምታጠሩ፥ ወዮላችሁ።አንተ ዕውር ፈሪሳዊ፥ ውጭው ደግሞ ጥሩ እንዲሆን አስቀድመህ የጽዋውንና የወጭቱን ውስጡን አጥራ።እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውጭ አምረው የሚታዩ በውስጡ ግን የሙታን አጥንት ርኩሰትም ሁሉ የተሞሉ በኖራ የተለሰኑ መቃብሮችን ስለምትመስሉ፥ ወዮላችሁ።እንዲሁ እናንተ ደግሞ በውጭ ለሰው እንደ ጻድቃን ትታያላችሁ፥ በውስጣችሁ ግን ግብዝነትና ዓመፀኝነት ሞልቶባችኋል  እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ የነቢያትን መቃብር ስለምትሠሩ የጻድቃንንም መቃብር ስለምታስጌጡና።በአባቶቻችን ዘመን ኖረን በሆነስ በነቢያት ደም ባልተባበርናቸውም ነበር ስለምትሉ፥ ወዮላችሁ።እንግዲያስ የነቢያት ገዳዮች ልጆች እንደሆናችሁ በራሳችሁ ላይ ትመሰክራላችሁ።እናንተ ደግሞ የአባቶቻችሁን መስፈሪያ ሙሉ።እናንተ እባቦች፥ የእፉኝት ልጆች፥ ከገሃነም ፍርድ እንዴት ታመልጣላችሁ?ስለዚህ፥ እነሆ፥ ነቢያትንና ጥበበኞችን ጻፎችንም ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ትገድላላችሁ ትሰቅሉማላችሁ፥ ከእነርሱም በምኵራባችሁ ትገርፋላችሁ ከከተማም ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፤ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችሁ ዘንድ።እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ በዚህ ትውልድ ላይ ይደርሳል።ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም።እነሆ፥ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል።እላችኋለሁና፥ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም።