ESMEBEFKADU

Monday, September 24, 2012

ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።ገላ6፤14

"ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።"ገላ6፤14

መስቀል መመኪያችን ነው።
የቤተክርስቲያን ልጆች መስቀልን የምንሳለመው፤የምናከብረው፤የምንሳለመው፤የምንሰግደው፤መመኪያችን ስለሆነ ነው።መስቀልን በአንገታችን ላይ የምናጠለጥለው በልብሳችን ላይ እንደ ጌጥ የምናደረገው መስቀል መመኪያችን ስለሆነ ነው።በመስቀል መመካት የተማርነው ከቅዱሳን ነው።"ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።"ገላ6፤14 በማለት ቅ/ጳውሎስ ተናግሮል።ከዚህ የተነሳ ነው እኛ ኢትዮጲያን በየትኛውም ዓለም ብንኖር መስቀልን መመኪያ አድርገን የምንጕዘው።
በመስቀል መመካት፤መባረክ፤መስገድ፤ለአለሙ ሞኝነት ይመስለዋል።1ኛቆሮ1፤18"የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።"ነገረ መስቀሉ የ እግዚአብሔር ሀይል የሚገለጥበት መሆኑን ቅዱስ ጳውሎስ ነግሮናል።ለቅዱስ መስቀሉም መስገድ እንደሚገባን ይነግረናል።መዝ13፡7"እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን።"ጌታችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእለተአርብ በመስቀል ላይ ተሰቅሎልና።
ጠላታችንንም ድል የምናደርግበት በመስቀል ነው።"ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ፥ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው። "መዝ59፤4 ምልክት የተባለው የመስቀል ምልክት ነው።በመስቀል ከሰይጣን እንደምንድን ሲነግረን ነው።
እርግማችን ተወግዶ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ ይሰጠን ዘንድ በመስቀል ተሰቀለ ።ስለዚህ መስቀል እርግማናችንን አጥፍቶ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ ይስጠናል።
መስቀል ዲያቢሎስ የተሸነፈበት የተዋረደበት ነው።"ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው። "ኤፌ2፤16 ጥልን ወይም ጸብን በመስቀሉ ገደለ ሲል፡- ጥልን ወይም ጸብን የሚዘራና የሚያመጣ ዲያቢሎስን ገደለ ሲል ነው።ዲያቢሎስ ሰውን ከ እግዚአብሔር ሁል ጊዜ ያጣላል ስለዚህ ነው ጥልን በመስቀሉ ገደለ ያለው።

መስቀሉን ስናይ እ ገዚአሔር ምን ያህል እንደወደደን እናውቃለን እስከ መስቀል ሞት ድረስ ወዶናልና።

ሰውና መላእክት የታረቁት በመስቀል ላይ በተፈጸመ ቤዛነት ነው።


የመስቀሉ ረድኤት በረከት በእኛ ላይ ይደር።


ደመራ በ5 ክርስቲያኖች ሲደመር


መስከረም 16 ቀን 2004 ዓም ነው በሰሜን የኢትዮጲያ ክፍል በሰሜን ውሎ ውልድያ ከተማ::ከጧቱ 11ስዓት ነው  የወፎቹ ዜማ ከጧቱ ብርድ ጋር ተቀላቅሎ ውስጣችን ዘልቆ ይሰማናል::እንደሌሎቹ ተጓዦች እኔ ና 3 ጓደኞቼ በረንዳ ላይ ምንጣፍ ተነጥፎልን ነበር ያደርነው ምክነያቱም የወ/ሮ በላይነሽ ቤት 60 ሰው የመያዝ አቅም ስሌላት በረንዳው ግን ለጥ ያለነው::መንፈሳዊ ጉዞ ታላቅ ፍቅርን ያስተምራል መተጋገዝን መረዳዳትን ያሰተምራል በጧት ተቀሳቅሰን ወደ ባሳችን አያመራን ነው::በባስ ውስጥ ያለነው 62 መንፈሳዊ ተጓዦች ነን ከአርባምንጭ ከተማ ተነስተን በደ/ሊባኖስ,ጣና ገዳማት ጎንደር , አክሱም , ደ/ዳሞ ,ቅ/ላሊበላ,ቅድስአርሴማ,... አገባደን ይህው ዛሬ እዚህ የደረስነው:: ሁሉም ከእንቅልፍ ተቀሳቅሶ ለጉዞ ተዘጋጀ ::እንደተለመደው በባሱ ውስጥ ጸሎት ለማድረግ ቦታ ቦታችንን ይዘናል::የጉዛችን አስተባባሪ ዓለሙ እይደጋገመ የቀሩ እናቶችን በመደገፈ ወደ መኪናው ያስገባል::ጉዛችን በጽሎት እንደተለመደው ተከፈተ በአባ ቦረዳ (ቆሞስ አባ ገ/ማርያም) ከዝያም በመቀጠል ተዓምረ ማርያም ተነበበ::የ አባ ቦረዳ የተዓምር አነባበብ ቅላጼው ለየት ያለና የሚማርክ ነው በ እውነት ውስጤን ይነካኛል ለዚህም ነው ሁልጊዜ ተዓምር ሲነበብ መጽሃፉን ለአባ ለመያዝ የሚቀድመኝ የለም::አባን በማየት ብቻ በጣም ብዙ ትምህርት ማግኘት ይቻላል እኔ ነኝ በዚህ ጉዞ አባ ምን ያህል እንዳስተማሩኝ የማውቀው::ስለ አባ ለማወቅ ቀርቦ ያያቸው ሰው ያውቀዋል ምስክሩም እሱ ነው::አባን እግዚአብሔር ይጠብቅልን::ቀጥታ ጸሎቱ እንዳበቃ ወደ ማመጫ ተክለሐይማኖት ጉዞ አደረግን::ስለ ማመጫ ተክለሐይማኖት በሌላ ጊዜ በሰፊው ብተርከው ሳይሻል አይቀርም::ወደዛሬ ጉዳዬ ስመጣ የማመጫ ጉዞ ቀትር ላይ ከተጠናቀቀ በኃላ ነው ሁለተኛ የ ደመራ ፕሮግራም ወደ ሐራ ማርያም ያደረግነው::ሐራ ትንሽ ከተማ ስትሆን የከተማዋ ነዋሪዎች በሙሉ ከ 5 ክርስቲያን በስተቀር ሙስሊም ናቸው::ሐራ ማርያም ከተማው መሐል ጉብ ብላ በአህዛብ መካከል ነግሳለች ይህንን በማሰብ ነበር የጉዛችን አስተባባሪ ደመራን ከእነሱ ጋር እንድናከብር ያመቻቹልን ጉዞ ወደ ሐራ ማርያም::መኪናችን ከተማው ሲገባ በዝማሬ ነበር ሁሉም ምዕመን ነጭ በነጭ ልብሰናል ዝማሬው አላቋረጠም::የከተማው ነዋሪዎች ገርሟቸው በግርምት ይመለከቱናል::በከተማው መኃል በዝማሬ ታጅብን ወደ ቤተክርስቲያኑ አመራን አዲሱ ቤተክርስቲያን ለመስራት ከተጀመረ ዘመን የለውም በተለያየ ምክነያት ሳይፈጽም ቀርቶ አሁነም እያየነው ነው:: እነዚያ በሰቆቃ የነብሩ በብቸኝነት የነበሩ ምዕመናን ከደስታቸው ብዛት በዕንባ ተቀበሉን የሚያደርጉልን ጠፋ::1 ዲያቆን እና 1ካህን ነው ያሉት ከቤተመቅደስ ነዋየቅዱሳቱን ይዘው ወጡ ቃጭል ተመታ መስቀልም ተያዘ ጉዞ ወደ መስቀል አደባባይ(አንድ የክርስቲያን ግቢ ውስጥ) ደመራ ተደመረ ምስባኩም ተሰበከ በአባ ቦረዳ ጣዕምያለው አጥንትን የሚያለመልም ትምህርትን ተማርን ደመራው ተለኮሰ ዛሬ 67 ሆነን ደምራውን አክበርን::እንዴት ደስ ይልነበር በጣም እንጂ ደምራን ከ ነዚያ ምዕመን ጋር ማሳለፍእጅግ ደስ ያሰኛል ወገን አጥተው በብቸኘነት ካሉ እንድዚህ አየንት ችግር ያለባቸው ደምራን ጥምቀትን የማያክብሩ ስንት ደብሮች ስንት ገዳማት በችግር ምክነያት እንደታጓሉ... ቤት ይቁጠረው እንዲህ አይነት ችግር ያሉበት ቦታዎች ::በዚህን ጊዜ ነበር የ አዲስ አበባው መስቀል አደባባይ አልያም ጊሸን ደ/ከርቤ የሚከበረው ትዝ ያለኝ::በብዙ ምዕመን መሃል ሆኖ ማክበር ደስ ቢልም በትንሽ ሰዎችህ መሃል በ እንባ በተቀላቀለበት ስሜት ማክበር ደግሞ ስሜትን ያስደስታል እጅግም ደስ ይላል እነሱ በደስታቸው ሲለቅሱ ማየት እኛ ከእነሱ ጋር እግዚአብሔርን ስናመሰግን ስላዩ ብቻ ሲደስቱ ማየት እንዴት የሚገርም ክርስትና ነው::
ድሮ ደመራ በ 5ክርስቲያንች ሲደመር ነበር ባልፈው ዓመት በ 67 ሰው  ተከበሮል ዝንድሮስ እንዴት ያከብሩ ይሆን ???
እስቲ የዛሬ ዓመቱን ፊልምና ፎቶው ልጋብዛችሁና ልሰናበት በጽሎታችሁ አስቧቸው::










to watch the vidio on facebok use this link ይህንን ይጫኑ



Tuesday, September 11, 2012

እመቅደመ ዘመናት ዘመናዊ ደኅረ ዘመን ሀዲስ ኢየሱስ ናዝራዊ::"


የ እግዚአብሔር ሥራው እንዴት ድንቅ ነው?ዘመናት የሌለው ከዘመናት በፊት የነበረ ያለ እና ወደ ፊትም የሚኖር ፈጣሪያችን ዘመናትን አቀናጀን የ እግዚአብሔር ሥራው እንዼት ድንቅ ነው::እሰከዚህ ሰዓት አድርሶናልና ምስጋና ይገባዋል::
"
ከዘመናት በፊት አንተ ነበርክ ሁሉን አሳልፈህ ትኖራለህ::
እመቅደመ ዘመናት ዘመናዊ ደኅረ ዘመን ሀዲስ ኢየሱስ ናዝራዊ::"
እመቅደመ ዘመናት ዘመናዊ ደኅረ ዘመን ሀዲስ ኢየሱስ ናዝራዊ::"

አወዳ ዓመን በባዕድ አገር ማሳለፍ እንደምን ልብን ይነካል በተለይ አገር ቤትን ባሰብኩኝ ቁጥር በአዕምሮዬ ብዙ ነገር ይመጣል የአውዳመት ሽታውም ይሸታል::በባዕድ አገር ወዼት አለ የ አወዳመት ሽታው? ወዴት አለ እንጀራ እና ወጡ ወዴት አለ ጣላ እና ጠጁ ወዴት አለ ዘመድ ጥየቃው ወዴት አለ የቤተሰብ ስብስቡ ወዴት አለ የቤተሰብ ስብስቡ ይህንን ባሰብኩኝ ቁጥር ወደ አገሬ በርሬ በሃሳብ ሄድኩኝ ከእናት አባቴ ጋር በላሁኝ ጠጣሁኝ ከጎደኞቼ ጋር ተጫወትኩ ደስም ተሰኘሁኝ::ከሃሳቤ ስነቃ እንባን በአይኔ አገኜሁኝ::


መልካም አወዳመት