ብዙ ፃድቃን ብታይም በዘመኖ ኢትዮጽያ
እንዳንተ አላየችም ሐዲስ ሐዋርያ
የብዙወች አባት መምህር መጠጊያ
ፃድቁ ተወልደ ከፀጋ ዘአብ ከእግዚሐርያ።
ቅዱስ ሚዳኤል ሊቀ መላእክት
ይመራውም ነበር ከኃላ ከፊት።
ምድራዊ መላእክ የመረጡት ስላሴ
የዓለም ቡራኬ ዳግማዊ ሙሴ
አለምን የናቀ ፅኑ መነኩሴ።
ፀጋ የተሰጠው የድህነት የፈውስ
ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ።
የዓለም ፀሀይ የገዳም መብራት
የእቲስ አንበሳ ተክለሃይማኖት።
ገድልህ ሲነበብ ታምርህ ሲነገር
እፁብ ድንቅ ያሰኛል የተሰጠህ ክብር።
ጠንቆይ አጋንቱን በእምነት ደመሰሰ
ወንጌልን አስተምሮ ፍቅር አነገሰ።
ብርሃን ፈንጣቂው የጨለማ ጠላት
የድህ ድል ምድራዊ ሀብት።
የፀሎቱ ሀይል ጥልቅ ነው ሚስጥሩ
ስድስት ክንፍ አወጣ ቢቆረጥ አንድ እግሩ።
ተነጥቆ ወደ ሰማይ በአምላክ ተባርኳል
በሱራፌል ተርታ ቅዱስ ቅዱስ ይላል።
ገዳምህ ተባርኳል በእየሱስ ክርስቶስ
ምህረት ይታፈሳል በደብረ ሊባኖስ።
ስለ ሀይማኖቱ ከወርቅ የነጠረ
በሰማይ በምድር ተክሌ ከበረ።
ቃልኪዳንህን እኛም እናምናለን
አማልደን አደራ ከቸር አምላካችን
ዋስ ጠበቃ ሁነን ተክልዬ አባታችን።
ምንጭ :http://www.youtube.com/watch?v=mgqZENrY7oY