ESMEBEFKADU

Tuesday, May 1, 2012

አዲስ ሐዋርያ ብርሃን ዘኢትዮጲያ አባታችን ተክለሐይማኖት


ብዙ ፃድቃን ብታይም በዘመኖ ኢትዮጽያ 
እንዳንተ አላየችም ሐዲስ ሐዋርያ
የብዙወች አባት መምህር መጠጊያ
ፃድቁ ተወልደ ከፀጋ ዘአብ ከእግዚሐርያ።
ቅዱስ ሚዳኤል ሊቀ መላእክት 
ይመራውም ነበር ከኃላ ከፊት።
ምድራዊ መላእክ የመረጡት ስላሴ
የዓለም ቡራኬ ዳግማዊ ሙሴ
አለምን የናቀ ፅኑ መነኩሴ።
ፀጋ የተሰጠው የድህነት የፈውስ
ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ።
የዓለም ፀሀይ የገዳም መብራት 
የእቲስ አንበሳ ተክለሃይማኖት።
ገድልህ ሲነበብ ታምርህ ሲነገር
እፁብ ድንቅ ያሰኛል የተሰጠህ ክብር።
ጠንቆይ አጋንቱን በእምነት ደመሰሰ
ወንጌልን አስተምሮ ፍቅር አነገሰ።
ብርሃን ፈንጣቂው የጨለማ ጠላት
የድህ ድል ምድራዊ ሀብት።
የፀሎቱ ሀይል ጥልቅ ነው ሚስጥሩ
ስድስት ክንፍ አወጣ ቢቆረጥ አንድ እግሩ።
ተነጥቆ ወደ ሰማይ በአምላክ ተባርኳል
በሱራፌል ተርታ ቅዱስ ቅዱስ ይላል።
ገዳምህ ተባርኳል በእየሱስ ክርስቶስ
ምህረት ይታፈሳል በደብረ ሊባኖስ።
ስለ ሀይማኖቱ ከወርቅ የነጠረ
በሰማይ በምድር ተክሌ ከበረ።
ቃልኪዳንህን እኛም እናምናለን
አማልደን አደራ ከቸር አምላካችን 
ዋስ ጠበቃ ሁነን ተክልዬ አባታችን።




ምንጭ :http://www.youtube.com/watch?v=mgqZENrY7oY

Monday, April 16, 2012

እኔስ በሃይማኖቴ እኔስ በእግዚአብሔር እመካለሁኝ ዓይኖቼ ማዳኑን አይተዋልና::


ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን     በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰርዎ ለሰይጣን                  አግዓዝዎ ለአዳም
ሰላም                                እምይእዜሰ
ኮነ                                   ፍስሐ ወሰላም


እንዼት ያስደስታል ይህንን በትንሣዔ ማየት ምንኛ ልብን ያስደስታል ከቅዱሳን መላዕክት ጋር ምስጋናን ማድረስ ...

ትንሣዔህን ለምናምን ለኛ ብርሃንን ላክልን ወደ እኛ


ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት አትመረምር እጅግ ጥልቅ ናት::

Monday, April 9, 2012

ለከ ኃይል ክብር ወስብሓት ወዕዘዝ ለዓለመ ዓለም

"ለከ ኃይል ክብር ወስብሓት ወዕዘዝ ለዓለመ ዓለም።አማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሓት ወዕዘዝ ለዓለመ ዓለም።ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይል ክብር ወስብሓት ወዕዘዝ ለዓለመ ዓለም።ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብል በአኰቴት።"አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ..............."
ትርጉም፡-ኃይሌ መከታዬና ረዳቴ ለኾንከው ለአንተ ለአምላኬ ለአማኑኤል ለጌታዬ ለኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ክብርና ምስጋና ጽናትም ለዘላለም የአንተ ናቸው።እያልኩ"አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር ስምህም ይቀደስ............"
ይህን ሊንክ በመጫን ሙሉ ጸሎቱን ማዳመጥ የችላሉ
http://xa.yimg.com/kq/groups/12497888/1529139576/name/TheChantedPartofHolyWeekPrayers.mp3
ስብሓት ለእግዚአብሔር ኪያነ ዘፈጠረ ከመናምልኮ!
ስብሓት ለማርያም እመ አምላክ ንግሥትነ ወእምነ!
ስብሓት ለመስቀለ ክርስቶስ ዕፀ መድኃኒት፤ኃይልነ፤ወጸወንነ።
ትርጉም፡-
"እርሱን እናመልከው ዘንድ እኛን ለፈጠረ እግዚአብሔር ምስጋና ይጋባል።"
"አምላክን ለወለደች ለንግሥታችንና እናታችን ድንግል ማርያም ምስጋና ይጋባል"
"ኃይልና ጋሻ፤መድኃኒትም ለኾነን ለክርስቶስ በእንጨት ላይ ለመስቀሉ ምስጋና ይጋባል"


Wednesday, April 4, 2012

ኢየሱስ ክርስቶስ ካህኑ ለዓለም ንጉሠ ፅዮን ወንጉሰ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ


ኢየሱስ ክርስቶስ ካህኑ ለዓለም ንጉሠ ፅዮን ወንጉሰ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ
Jesus christ etrnal priest king of zion king of kings of Ethiopia

መድኃኒያለም ክርስቶስ በቀራኒዮ ስቁል
በለኒ መሃርኩከ በለኒ መሃርኩኪ
በእንተ ማርያም ድንግል እስመሔር አልቦ እንበሌከ ቃል


መድኃኒያለም የቸርነቱን ሥር ይስራልን::

ስኳር ገዳም ገባ

እያንገራገረ ህዝቡ እያባባ 
አበው እያዘኑ ወጣት እያነባ
 እየተቃወሙ እየጮሁ እነ አባ 
ዜናው በዓለም ዓቀፍ እየተስተጋባ 
ድንገት ሳይታሰብ ስኳር ገዳም ገባ
ከፍ ከፍ ብሎ ለዚያውም ዋልድባ 
ሲጠፋ ሲሰወር ሲደበቅ ቆይቶ 
በአቋሙ ጠንክሮ በአቋሙ ጸንቶ
አመክሮ ሳይዝ ድንገት ገዳም ገብቶ 
ጣፋጭ የነበረው ሊመር ነው ከቶ 
ለሱ የሚስማማ ስንት ቦታ ሞልቶ 
ስኳር እሳት ሆኖ ከገበያ ጠፍቶ 
ሊቀመጥ ነው አሉ መቃብር ቤት ገብቶ 
ምን ይውጥሽ ይሆን ከእንግዲህ መርካቶ 
አባቶች ምን አሉ በዋልድባ ያሉ
በአባቶች አጽም ላይ ሸንኮራን ሲተክሉ
ከተቀበረበት እየፈነቀሉ
በደም የበቀለ ሸንኮራ ሊበሉ
በውሳኔ ጸንቶ 
ረ እግዚኦ በሉ!
ይሄስ ጥሩ አይደለም
ከአቅም በላይ ሆኖ ህዝቡ ቢበደለም
አባቶች ዝም በሉ ይረሱት ግድየለም
ዋልድባ በጾሙ ምነው ተፈተነ
በገዳሙ ልማድ ትንሽ ከታዘነ
ጽሎቱ እንደወጉ ከተከናወነ
ውሎ አድሮ ይሟሟል ስኳር ስለሆነ


ከአዜብ ሮባ 



ምንጭ http://www.zehabesha.com/?p=5502

Monday, April 2, 2012

እስኪ ጎበዝ ቆም ብለን እናስብ ኢትዮጲያ ጣልያንን ያሸነፈችው ኃይለኛ ጣር ስላላት አይደለም ኃይለኛው አምላክ የሚማጽን ቅዱሳን ስላላት እንጂ


ኢትዮጲያዊ ሃብቱ ሳይሆን እምነቱ ና ባህሉ  የአባቶቹ ጽሎት ነው እያኖረው ያለው::አመንም አላመንም የኛ በሰላም ውሎ ማደር ጤንነት ኑሮ በኛ ሃይል ብቻ የመጣ ሳይሆን እንደ እኛ አጥንትና ደም ሳይቆጥሩ ሌትከቀን በሚጸልዩት አባቶቻችን ጭምር የመጣ ነው::እስኪ ጎበዝ ቆም ብለን እናስብ ኢትዮጲያ ጣልያንን ያሸነፈችው ኃይለኛ ጣር ስላላት አይደለም ኃይለኛው አምላክ የሚማጽን ቅዱሳን ስላላት እንጂ::     ....

አበው እንዲህ ይላሉ ''መንግስት ሊወድቅ ሲያምረው ከታቦት ጋር ይጣላል''
...
"መብላት ቢያቅታት በተነችው"
...
ሳይቃጠል በቅጠል የዋልድባ ጉዳይ



Tuesday, March 13, 2012

አንተ ባለህበት


ምንም በደል  ቢኖር
         
ኃጢአትም ቢበዛ
የመታዘዝ ፍሬ
        
ከሰዎች ቢታጣ
የፅድቅ ሥራ  ጠፍቶ
         
አመፅ ቢበረታ
አንተ ባለህበት ---
          
በዚያ ምህረት አለ
          
ኩነኔም  የለበት
የሚያስደንቅ ማዳን
          
ፍቅር የሞላበት
የይቅርታ ጉዞ
           
ፅድቅ የሰፈነበት
---
ምን ጠላት ቢበዛ
           
ኃይሉም ቢበረታ
ቀንበሩም  ቢፀና
              
ቢበዛም ሁካታ
አስፈሪ ነበልባል
              
እጅግ ቢንበለበል
ውኃውም ቢፈላ
             
ቢፍለቀለቅ በኃይል
የኤርትራ ባህር
              
በሰፊው ቢንጣለል
ወደ አንበሶች ጉድጉዋድ
               
ቢኖር እንኳን መጣል
አንተ ባለህበት ---
             
ጠላት ይሸነፋል
የእብሪቱ  ድልድይ
              
በቃልህ ይናዳል
ነፃነት ታውጆ
             
ቀንበሩም ይነሳል
ፍል ውሃው ቀዝቅዞ
              
እሳቱም ይጠፋል
ባህሩ እንደተራራ
             
ቀጥ ብሎ ይቆማል
ጠላት ከነጀሌው 
              
በውሃ ይበላል
              
ውሃ ውስጥ ይሰጥማል
የአናብስቱም አፍ
               
በኃይልህ ይዘጋል
--- 
ነውጡ እጅግ ቢያይል
               
ማእበል ቢነሳ 
ተስፋ መቁረጥ ነግሶ
                
ቢበዛም አበሳ
አንተ ባለህበት ---
                
ይታዘዛል ባህሩ
ነውጡም ያጣል ኃይሉን
               
ጸጥ ይላል ማእበሉ
---
አሳዎች በባህር
               
አንዳችም ባይኖሩ
መረቡም ባይሞላ
               
ድካም ቢሆን ትርፉ
አንተ ባለህበት
               
ማጣት የለም ከቶ
ረሃብ ይወገዳል
                
አሳው ተትረፍርፎ
                
መረቡም ሞልቶ
---
ህመም ደዌ ጸንቶ
                 
ሕይወት ብትደበዝዝ
አስታማሚ ጠፍቶ
                  
ባይኖርም የሚያግዝ
አንተ ባለህበት ---
                
መድሃኒት መች ጠፍቶ
የማያየው ሁሉ
                  
ይመለሳል አይቶ
በደስታ ይቦርቃል
                  
ለምፃሙ ሰው ነፅቶ 
ዲዳው ይናገራል
                 
ይጮሃል አብዝቶ
---
ምን ሞት ቢበረታ
                  
ቢያይል ፍርሃቱ
ብቸኝነት ነግሶ
                  
ቢበዛ ጭንቀቱ
አንተ ባለህበት ---
            
ሞት ስልጣኑን ያጣል
ማንቀላፋት የለም
             
የሞተም ይነሳል
ሀዘኑ በደስታ
              
ሞትም በትንሣኤ
              
በአንተ ይለወጣል
ስለዚህ ጌታ ሆይ
             
በአንተ ሁሉ ካለ
የአንተ ልሁንና
             
ሁሉን ላግኝ  ከአንተ

መቅደስ አያሌው  (ከደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን)